Skip to main content
Resources

ጋዜጣዊ መግለጫ፥ ICANN የአፍሪቃ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማበልጸግ ተነሳሽነት ጀምሯል

ለበለጠ የበይነመረብ መዳረሻ፣ ግንኙነት ለመተባበር የዲጂታል አፍሪቃ ኅብረት

ይህ ገፅ በሚከተለው ቋንቋ ይገኛል:

ዲሴምበር 1, 2022 አዲስ አባባ ኢትዮጲያ – የበይነመረብ ኮርፖሬሽኑ ለተመደቡ ስሞች እና ቁጥሮች (The Internet Corporation for Assigned Names and Numbers (ICANN)) ዛሬ በይነመረብን በአፍሪቃ ለማስፋፋት ያለመ ተነሳሽነት ለዲጂታል አፍሪቃ ኅብረት ጀምሯል። በ ICANN ታስቦ፣ ኅብረቱ ተጨማሪ አፍሪቃዎችን ወደ መስመር ለማስመጣት ፈጣን እና ድህንነቱ የጠበቀ መሠረተ ልማት ለመገንባት ቁርጠኝነት ያለው ተመሳሳይ-ሐሳብ ያላቸው ድርጅቶች ኪዳን ነው።

በፕላኔቱ ለወጣት ሕዝብ ቤት የሆነ፣ 70 በመቶው ከ 30 በታች ዕድሜ ያላቸው፣ አፍሪቃ በዓለም ላይ የበይነመረብ የደረጃ ዕድገት ፋጣን ዕድገት ካላቸው አንዷ ናት። የበይነመረብ ግንኙነቱ የመስመር ላይ አገልግሎቶች በግኝት ባህሪ የሚቀበሉ እና የሚጠቀሙ ዲጂታላዊ አዋቂ፣ ወጣት እና የተማሩ የከተማ የስራ ኅይል – ከ 1.2 መቶኛ በ 2000 እስከ 43 መቶኛ በ 2021 – በፈጣን ዕድገት በማደግ ላይ ነው።

"የዲጂታል አፍሪቃ ኅብረቱ በተለያዩ የድርሻ አካላት ለአዲስ የእገዛ እና ትብብር መንገዶች ትብብር ዕድል ይሰጣል፣" ይላል የ ICANN ፕረዚደንት እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጎራን ማርቢ። "ኅብረቱ በ ICANN ሐሳብ የተነሳ ቢሆንም፣ ስኬቱ የሚመረኮዘው ከ ሌሎች ድርጅቶች ጋር በሚደረግ የተባበረ ስራ ነው – አከባቢያ፣ ክልላዊ ወይም ዓለም አቀፋዊ የሆኑ – የአፍሪቃን የበይነመረብ መሠረተ ልማት፣ የበይነመረብ መጠን ለመጨመር፣ የበይነመረብ ደህንነት የሚደግፍ እና በባለ ብዙ የድርሻ አካል የፖሊሲ ስራ ልማት ከአፍሪቃ የተሳታፊነት ደረጃ ለማሳደግ በዓላማቸው የተባበሩ ናቸው።"

ኅብረቱ ቴክኒካዊ ዓቅምን ለመገንባት እና በራሳቸውን ቋንቋ እና ጽሁፍ በመጠቀም በይነመረቡን ለመዳረስ ሰዎችን በማስቻል ኢንተርፕረኒዋሊዝም ለማበረታታት ያለመ አዲስ አሰራርን በተጨማሪ ያሳድጋል። ይፋዊ መጀመሩን በ 17ኛው ዓመታዊ የበይነመረብ አስተዳደር ፎረም በጋዜጣዊ ኮንፈረንስ ወቅት በተካሄደ ጊዜ፣ ኅብረቱ አስቀድሞ ዓላማዎቹን ለመከታተል ተግባራትን አውጥቶታል።

የጎራ ስም ስርዓት (DNS) መሠረተ ልማት በአፍሪቃ በጣም ቀልጣፋ፣ ፈጣን ዕድገት ሊያስተናግድ የሚችል ለማድረግ፣ ኅብረቱ በ ICANN የሚተዳደር ዋና አገልጋይ (IMRS) ክላስተር መትከሉን ባለፈው ወር በኬንያ አስታውቋል። በሚቀጥለው ዓመት ሌላ ክላስተር በአፍሪቃ ለሁለተኛ ቦታ ታቅዷል። እነዚህ ክላስተሮች በሌሎች የዓለም ክፍል ባሉ የአውታረ መረቦች እና አገልጋዮች ጥገኛ ከመሆን ክልላዊ የበይነመረብ ጥያቄዎችን በክልሉ ለመመለስ ያስችላሉ። የ IMRS ክላስተሮች በአፍሪቃ ውስጥ ሊደርስ ከሚችል የሳይበር ጥቃት ሊቀንሱ ይችላሉ።

"የኅብረቱ መነሳሳት በአፍሪቃ ውስጥ የበይነመረብ መሠረተ ልማት ለማጠናከር አንድ ደረጃ ሊያደርሰን ይችላል። ኅብረቱ የበለጠ የተጠበቀ DNS እና ተጨማሪ ደህንነቱ የጠበቀ የበይነመረብ መሠረተ ልማት በአፍሪቃ፣ ለማስቻል አስፈላጊ መሳሪያ ያቀርባል፣" ይላል አቶ ጆን ኦሞ፣ የአርሪቃ የቴሌኮሙኒኬሽን ህብረት ዋና ጸሐፊ። የኅብረቱ መመስረት በመገንዘብ ልክ አህጉሩ የበይነመረብ ዕድገት በአፍሪቃ ውስጥ ከአሁኑ 43% ወደ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ደረጃዎች ለማሳደግ በመጠባበቅ ላይ ያለ አሁን ዋና ግንባር ቀደም የሆኑ በብዙ የመስመር ላይ ስርዓቶችን መተማመን የማሳደግ አስፈላጊ ሚና ይጫወታል፣ ።

የኅብረቱ ትኩረት ትርጉም ያለው ግንኙነት በአፍሪቃ ውስጥ ለመፍጠር ነው። ኅብረቱ ዲጂታል አካታች ላማስቻል እና የአካባቢ ይዘት እና ንግዶችን ዕድገት ለማነሳሳት ዕድሎችን በመፍጠር በይነመረቡን በአፍሪቃ ውስጥ የበለጠ ለመልመድ በመስራት ይጀምራል። የቁመት ወይም የጽሑፍ በሁሉም በበይነመረብ-የሚሰሩ መተግበሪያዎች፣ መሳሪያዎች እና ስርዓቶች ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችል ምንም ያክል ቢሆንም፣ ሁሉም ቅቡል የጎራ ስሞች እና የኢሜይል አድራሻዎች የሚያረጋግጥ ለጥረቱ ዋና ቁልፍ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ወይም UA ነው። ከ UA፣ ቀድሞዉኑ የተገናኙ ሰዎች እና በመጪው ሊገናኑ የሚችሉ፣ በበይነመረብ ሊገናኙ እና አካባቢያዊ ይዘት በራሳቸው የተመረጡ ቋንቋዎች እና ጽሑፎች መዳረስ ይችላሉ።

ኅብረቱ ይህን ሊገታ የሚችልበት አንዱ መንገድ ኢሜይል እና ሌሎች ስርዓቶች በከፍተኛ ትምህርት UA-ዝግጁ የማድረግ ያለመ በአፍሪቃ ዩኒቨርሲቲዎች ማህበር የሚመራ ፕሮጀክት ነው። ይህ ጠቃሚ እና ለሁሉም ሰዎች ለማሰልጠን ሁለቱም በይነመረብ የማረጋገጥ መነሻ እርምጃ ነው።

ይህ ለአፍሪቃ አስፈላጊ እና የሚያስደስት ተነሳሽነት ነው። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቴክኒክ ዓቅም በመላው አህጉር ማሻሻል ለዲጂታል አፍሪቃ አስፈላጊ ነው፣" ይላል ኦሉሶላ ባንደለ ኦየዎለ፣ የአፍሪቃ ዩኒቨርሲቲዎች ማህበር ዋና ጸሓፊ። "የአፍሪቃየበይነመረብ ተጠቃሚዎች የእውነተኛ ኋላቀፍ፣ አካታች እና ብዙሐ-ቋንቋ በይነመረብ ለመስጠት አካል የመሆን ዕድል ተሳታፊ በመሆናችን ደስተኞች ነን።"

የዲጂታል አፍሪቃ ኅብረቱ መንግስታት፣ ክልላዊ እና ዓለም አቀፋዊ ድርጅቶች እና የአካባቢ የበይነመረብ ማህበረሰቡ ያጠቃልላል። የኅብረቱ የምርቃት አጋሮች የአፍሪቃ የአውታረ መረብ ማዕከል (African Network Information Centre)፣ አፍረጂስትራር ማህበር (AfRegistrar Association)፣ የአፍሪቃ ከፍተኛ ደረጃ ጎራ (Africa Top Level Domain Organization)፣ የአፍሪቃ የቴሌኮሙኒኬሽን ማህበር (Africa Telecommunications Union)፣ የአፍሪቃ የዩኒቨርሲቲዎች ማህበር (Association of African Universities)፣ የፈረንሳይ የበይነመረብ ስም ማስወጣት ኮርፖሬሽን ማህበር (Association Française pour le Nommage Internet en Coopération) ዓለም አቀፍ የቴሌኮሙኒኬሽን የኅብረት-ልማት ክፍል (International Telecommunication Union-Development Sector) እና የአውታረ መረብ ጀማሪ ሃብት ማዕከል (Network Startup Resource Center) ያካትታል።

ተጨማሪ መረጃ በ www.coalitionfordigitalafrica.africaይገኛል።

ስለ ICANN

የICANN ተልዕኮ የተረጋጋ፣ ደህንነቱ የጠበቀ እና አንድ የሆነ ሁላቀፍ በይነመረብ ለማረጋገጥ ለማገዝ ነው በበይነመረብ ወደ ሌላ ሰው ለመድረስ በኮምፒዩተርዎ ወይም ሌላ መሳሪያ ላይ አድራሻ ስም ወይም ቁጥር መተየብ አለብዎ። ያ አድራሻ ልዩ መሆን አለበት፣ እናም ኮምፒዩተሮች እርስበርሳቸው የት እንደሚገናኙ ያውቃሉ። ICANN እነዚህን ልዩ መለያዎች በመላው ዓለም ለማስተባበር እና ለመደገፍ ያግዛል። ICANN በ 1998 እንደ ትርፋማ ያልሆነ ህዝባዊ ጥቅማጥቅም ኮርፖሬሽን እና በሁሉም ዓለም ያሉ ተሳታፊዎች ያሉበት ማሕበረሰብ የቆመ ነበር።

የሚዲያ አድራሻ

Luna Madi
Communications Director, EMEA
Internet Corporation for Assigned Names and Numbers (ICANN)
ሞባይል፦ +90 (533) 031 35 05
ኢሜይል፦ luna.madi@icann.org
ወይም press@icann.org

Domain Name System
Internationalized Domain Name ,IDN,"IDNs are domain names that include characters used in the local representation of languages that are not written with the twenty-six letters of the basic Latin alphabet ""a-z"". An IDN can contain Latin letters with diacritical marks, as required by many European languages, or may consist of characters from non-Latin scripts such as Arabic or Chinese. Many languages also use other types of digits than the European ""0-9"". The basic Latin alphabet together with the European-Arabic digits are, for the purpose of domain names, termed ""ASCII characters"" (ASCII = American Standard Code for Information Interchange). These are also included in the broader range of ""Unicode characters"" that provides the basis for IDNs. The ""hostname rule"" requires that all domain names of the type under consideration here are stored in the DNS using only the ASCII characters listed above, with the one further addition of the hyphen ""-"". The Unicode form of an IDN therefore requires special encoding before it is entered into the DNS. The following terminology is used when distinguishing between these forms: A domain name consists of a series of ""labels"" (separated by ""dots""). The ASCII form of an IDN label is termed an ""A-label"". All operations defined in the DNS protocol use A-labels exclusively. The Unicode form, which a user expects to be displayed, is termed a ""U-label"". The difference may be illustrated with the Hindi word for ""test"" — परीका — appearing here as a U-label would (in the Devanagari script). A special form of ""ASCII compatible encoding"" (abbreviated ACE) is applied to this to produce the corresponding A-label: xn--11b5bs1di. A domain name that only includes ASCII letters, digits, and hyphens is termed an ""LDH label"". Although the definitions of A-labels and LDH-labels overlap, a name consisting exclusively of LDH labels, such as""icann.org"" is not an IDN."